2/13/2017

ሰላም ፡ ለናንተ ይሁን ፥ሶፊያ ሽባባው


ሰላም ፡ ለናንተ ይሁን
ካቶሊክ ፤ ኦርቶዶክስ ፤ ሙስሊም ብትሆን ጴንጤ
የሰላምህ ምስጢር ይህ አይደለም ዛሬ፤
የደህንነት መንገድ ዋስትናው መያዣው፤ 
ኢየሱስን አምኖ መከተል ብቻ ነው
   
ሶፊያ ሽባባው




9/11/2009

አምላኬ አይተወኝም (አንድነት ለማ)


የዳዊት መዝሙር።
1፦ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2፦ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3፦ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4፦ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5፦ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6፦ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

8/04/2009

ውዳሴ ነ የሱስ (ሰሎሞን መንግስ)



ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።
እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።
ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና። መዝ 149፤3

2/24/2008

ምሕረትሀና ቸርነትህ (ምሕረት ኢታፋ)



ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም
እኖራለሁ። መዝ፡ 23-6

አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና። መዝ 25-6

WARRI WAAQA ዋሪ ዋቃ (ROOBAA AMAAN ሮባ አማን)

ረዳቴ (ፀሎት ስዩም )


ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
መዝሙረ ዳዊት 121

2/23/2008

ተራው የኔ ነው (ኤፍሬም አለሙ)

ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ ትንቢተ ዘካርያስ 4 7

ታለፈ ያ ዘመን (መስፍን ጉቱ)


"...መከራህንም ትረሳለህ
እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ። .." ኢዮብ 11 16

የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መዝሙር 2

2/19/2008

ሰልፉ የማነው ? (ሠናይት እንግዳ)


"እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል። ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ
አትፍሩ፥ አትደንግጡም።" መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 13-14

"እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።" መዝሙረ ዳዊት 20-7

ዞር በል አንተ ክፉ (ተመስገን ማርቆስ)

አልፈራም (የናዝሬት መዝመራን)

1/11/2008

visiters

Free Hit Counters